July 31, 2019

ፕሮስቴት ካንሰር (Prostate Cancer)

ፕሮስቴት ካንሰር (Prostate Cancer)

ፕሮስቴት በወንዶች የሰውነት ክፍል የሚገኝ ዕጢ ሲሆን ከሽንት ፊኛ ስር ተጠግቶ የሚገኝ አካል ነው፡፡ ከሽንት ፊኛ ሽንት ይዞ የሚወርደው ቱቦ በዚህ በፕሮሰቴት ዕጢ በኩል አልፎ ነው የሚሄደው፡፡ የዚህ ዕጢ ዋናው ተግባር ሴመን (semen) የተባለ ፈሳሽ ማመንጨት ነው፡፡ ይህ ፈሳሽ ደግሞ የወንዶች የዘር ሴሎችን (sperm ) ለመመገብና ለማመለስ ይረዳል፡፡ 
ፕሮስቴት ካንሰር የሚመጣው ከዚህ ፐሮስቴት ከተባለ ዕጢ የሚገኙ ሴሎች ከመጠን በላይና ከቁጥጥር ውጭ በሚያድጉበት ጊዜ ነው፡፡ የእድሜ ክልል ከ60 አመት ባላፋቸው በአብዛኛዎች ወንዶች ፕሮስቴት ካንሰር የሚከሰት ቢሆንም ከዕጢ ውጭ ተስፋፍቶ ካልተሠራጨ በስተቀር ከፍተኛ ጉዳት አያደርስም፡፡

፠አጋላጭ ሁኔታዎች

ዕድሜ
ሲጋራ ማጨስ
በቤተሰብ ውስጥ የህ ካንሰር ተከስቶ ከሆነ
ጤናማ ያልሆነ ስኳር እና ጮማ የበዛበት አመጋገብ ውፍረት

፠ምልክቶቹ፣

ከእምብርት በታች የህመም ስሜት፣ ከወገብ በታች ህመም ስሜት፣ ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት፣ ሽንት ሲሸኑ የህመም ስሜት፣ ቶሎ አለመውረድ ወይም ማስማጥ፣ ማቃጠል ወይም
መለብለብ፣ ደም በሽንት ወይም በዘር ፈሳሽ ወስጥ መታየት፣ በግብረስጋ ጊዜ ሕመም ስሜት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ክብደት መቀነስ

ፕሮስቴት ካንሰር ህክምና

ህክምናው ካንሰሩ እንደተገኛበት ደረጃ እንደበሽተኛው እድሜ ፤ እንደ እድሜ ዘመን እና ጠቅላላ በሽተኛው የሚገኝበት የጤንንት ደረጃ ወይም ሁኔታ የሚደረግ ነው፡፡