July 30, 2019

ማር_ለጤና... ለብ ባለ ውሀ

አንድ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃን በአንድ የሾርባ ማንኪያ ንጹህ ማር በደንብ አዋህዶ ጠዋት በባዶ ሆድ በመጠጣት የሚያገኟቸው የጤና በረከቶች :-
- ሳንባ ላይ የሚከማችን አክታ ያስወግዳል፤
- የጉሮሮ ቁስለትንና አደገኛ ጉንፋንን በመከላከል እና በማስወገድ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳብራል፤
- የሆድ እቃ እና የውስጥ ቁስለትን በማስወገድ ለበሽታ የሚያጋልጡ ጥገኛ ህዋሳት እንዳይራቡ ያደርጋል፤
- የሆድ ድርቀትን በመከላከልና በማለስለስ ለተስተካከለ

የሰውነት ሽግግር ይረዳል።
- ከዚህ ባለፈም መፀዳጃ አካባቢ የሚፈጠር ድርቀትንም መከላከል ያስችላል፤

- አጠቃላይ ሰውነትንና አንጀትን ንጹህ እና ፅዱ በማድረግ መርዘኛ ነገሮችን ከሰውነት ለማስወገድ ይረዳል፤
- ፈንገስን እና ባክቴሪያን በመከላከል ቫይረስ በሰውነት ውስጥ እንዳይከሰትና እንዳይከማች ያደርጋል፤
- የሚከሰትን የሽንት አለመቆጣጠር ስርአትን ማስተካከልም የዚሁ ውህድ ሌላው ጠቀሜታ ነው።
- ማር የኩላሊትን የማጣራት ተግባር በእጅጉ በማገዝ እና ስራውን ቀልጣፋ በማድረግ የሚፈጠረውን የጤና ጠንቅ የማስወገድ አቅም አለው።
- በዚህ ተግባሩም ኩላሊት መደበኛ እና የተስተካከለ ስራውን እንዲሰራ በማድረግ ጤናማ እንቅስቃሴን ይፈቅድልዎታል።
- ከዚህ ባለፈ ደግሞ ይህን የማር ብጥብጥ በመጠጣት እጅግ ማራኪና ፅዱ የቆዳ ገጽታንም ያላብስዎታል።
>> ከቻሉ ይህን ውህድ ማታ ላይ ከእራት በፊትም ቢጠጡት መልካም ነው።
>>ደግሞ ከቻሉ አሁኑኑ ሼር ያድርጉት፤ ሌሎችን ማሳወቅ ከስጦታዎች ሁሉ ይበልጣልና