July 30, 2019

በተደጋጋሚ ቶሎ ቶሎ ሽንትዎ እየመጣ ተቸግረዋል በምን ምክንያት እንደሆነ ያውቃሉ ?


በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ማለት ጤናማ ከሚባለው የሽንት መምጫ ጊዜ በበለጠ በተደጋጋሚ ሽንት የመሽናት ፍላጎትን ሲለማመዱ/ ሲተገብሩ ነው፡፡ ይህ ልምድ በቀን ወይም በማታ ሊሆን ይችላል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ማታ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ 

በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ሥራዎን፣ እንቅልፍዎንና አጠቃላይ ሠላምዎን ሊያስተጓጉል ይችላል፡፡ ስለዚህ የዚህን ችግር መነሻና ህክምናውን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ይሆናል ፡፡
 የዚህ ችግር መነሻ መንስኤ ምንድን ነው?

• የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን (Urinary Tract Infection)
በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በሆድና ዳሌ አካባቢ ህመም እንዲሁም ትኩሳት ካለብዎ በዚህ ኢንፌክሽን መጠትዎን አመላካች

ናቸው፡፡

• የስኳር በሽታ (Diabetes)

በተደጋጋሚ የመሽናት ፍላጎት ካለዎትና በጣም በርከት ያለ ሽንት የሚሸኑ ከሆነ በዓይነት አንድ ወይም ሁለት (Type 1 or 2) የስኳር በሽታ ተይዘው ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ ሽንት የሚሸኑበት ምክንያት ሰውነትዎ ትርፍ ግሉኮስን ለማስወገድ ስለሚሞክር ነው፡፡

• እርግዝና (Pregnancy)

በእርግዝና ወቅት ሽንት ቤትን በተደጋጋሚ መጎብኝት ይስተዋላል፡፡ ይህ ሁኔታ በደንብ የሚስተዋለው ደግሞ ጽንሱ በደንብ እየገፋ ይመጣና የሽንት ፌኛን ስለሚጫነው ነው፡፡

• የፕሮስቴት ችግር (Prostate Problem)

ዩሬትራ ሽንትን ከሰውነታችን የሚያስወግድ ቱቦ ነው፡፡ ነገር ግን ፕሮስቴት በመጠን ይተልቅና ይህን ቱቦ ሊዘጋው ይችላል፡፡ ፕሮስቴት ዩሬትራን ይጫነዋል በተጨማሪም የሽንት ፌኛ ግድግዳን እንዲቆጣ ያደርገዋል ይህም የሽንት ፊኛ እንዲጨማደድ ስለሚያደርገው መያዝ ያለበትን ያክል ሽንት እንዳይዝ
ስለሚያደርገው ለመሽናት እንቻኮላለን።

• ኢንተርስቲሺያል ሲስታይቲስ (Interstitial Cystitis)

ይህ ችግር በምን እንደሚከሰት ግልጽ አይደለም ነገር ግን በሽንት ፌኛና ዳሌ አካባቢ ህመም ያስከትላል፡፡ ሽንት ለመሽናት ከመቻኮል በተጨማሪ ሌሎች ምልክቶችን ሊያዩ ይችላሉ፡፡

• የሚያሸኑ መዳኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ (Diuretic Use)

ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚወስዷቸው ዲውሪቲክስ መድሃኒቶች በተደጋጋሚ ሽንት እንዲሸኑ ሊደርግዎት ይችላሉ፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች ብዙ ውሃ ከኩላሊትና ከሰውነትዎ እንዲወገድ ይረዱናል፡፡

• የነርቭ ጉዳት (Nerve Problems)

ወደ ሽንት ፊኛ የሚያመሩ ማንኛውም የነርቭ ጉዳት ሽንት በተደጋጋሚ እንዲሸኑ እንዲሁም ሽንትዎ በድንገት መቶ እንዲቻኮሉ ያስገድድዎታል፡፡

መልካም ጤንነት እንመኝሎታለን