July 31, 2019

ቀላል መፍትሄዎች ለጉንፋን


አብዛኛዉ የጉንፋን ህመም ያላቸዉ ሰዎች የህክምና ባለሙያ ማየት ሳያስፈልጋቸዉ በቤታቸዉ ሆነዉ እራሳቸዉን ማከም ይችላሉ፡፡ ለክፉ ጊዜ ስለሚሆነን ሼር እናድርገው..

እንፋሎት_መታጠን/መማግ፡-
ፎጣ/ማንኛዉንም ነገር ጭንቅላትዎ ላይ በመሸፈን እየፈላ ባለ ዉሃ እንፋሎቱን መታጠን፡፡ ይህ የመቆጥቆጥና የአፍንጫ መጠቅጠቅ ስሜቱን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
#ፈሳሽ_በብዛት_መጠጣት (የአልኮል መጠጥን አይጨምርም)፡- ዉሃ፣ ጁስ/የፍራፍሬ ጭማቂና ሞቅ ያለ ሾርባ በብዛት መዉሰድ የሚከሰትብዎንየፈሳሽ እጥረት ለመከላከል ይረዳል፡፡

#በቂ_እረፍት ማድረግ፡-

የበሽታ መከላከል አቅምዎን ለማጎልበትና ቫይረሱን መዋጋት እንዲችሉ

በቂ እንቅልፍ ያግኙ፡፡

በተጨማሪም….

• #መጉመጥመጥ፦ አፍን ወደ ላይ ቀና አደርጎ ከጀርባ ወደ ኋላ ገለል በማለት ጥቂት ውሃ ወደ ጉሮሮ በማፍሰስ መጉመጥመጥ የጉሮሮ መከርከርና ማቃጠልን ለመከላከል ይረዳል። ለዚህ ደግሞ 1 የሻይ ማንኪያ ጨውን ለብ ባለ አንድ ኩባያ ውሃ በመቀላቀል ወደ ጉሮሮ ማንቆርቆር እና መጉመጥመጥ። ከዚህ ባለፈም 1 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ውሃና ማርን አንድ ላይ በማድረግ ከውሃው ጋር ቀላቅሎ መጠቀም፤ ውሃው ግን ለብ ያለ እንጅ የሚያቃጥል መሆን የለበትም።

• #ሻይ_ በሎሚ እና በማር ቀላቅሎ መጠጣትም ይመከራል፤ ሻይን በሎሚ እና በማር መጠቀምዎ የአፍንጫ መደፈንና መታፈንን እና የጉሮሮ ህመምን ለማከም እንደሚረዳም ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሾርባ በተለይም የአትክልት ሾርባዎችን መውሰድም ይመከራል፥ በጉንፋኑ ምክንያት የሚፈጠረውን የአፍንጫ መዘጋት በመክፈት በአግባቡ ለመተንፈስ ስለሚረዳ። እንደ ቡና እና አልኮል ያሉ መጠጦችን ደግሞ ያስወግዱ።

• #ሙቀት፦ ሞቅ ባለ ውሃ ገላን መታጠብ የአፍንጫ መደፈንን ያስወግዳል። ጉንፋን በታመሙ ጊዜ በሙቅ ውሃ መታጠብ አልያም ውሃን በማፍላት በጎድጓዳ ሳህን በማድረግ በፎጣ ነገር ተከናንቦ መታጠን። ከዚህ ጋር ተያይዞ በዚህ ወቅት መድሃኒት ቤት የሚሸጡና ለጉንፋን ማከሚያ የሚረዱ ኢዩካሊፕተስ የሚባሉ ጠብታዎችን ውሃው ላይ በማድረግ መጠቀም። እንዲሁም የውሃውንና የጠብታውን ውህድ አፍንጫ ውስጥ ማድረግም መልካም ነው፤ ይህን ሲያደርጉ ግን አይንዎን መጨፈን ይኖርብዎታል።

• #ማር፦ በጉንፋን የተያዘ አዋቂ ሰው ማርን ከሻይ ጋር ቀላቅሎ እንዲጠቀም ይመከራል። እድሜያቸው ከአንድ አመት በላይ ለሆኑ ህጻናት ደግሞ ከመኝታ በፊት በጥቂቱ መስጠት፤ በመኝታ ሰዓት እንዳይስሉ ይረዳቸዋልና።

ላይክና ሼር