July 31, 2019

የጆሮ ማዳማጫ (Earphone) አዘውትሮ መጠቀም እና ድምፅ ከፍ አድርጎ መስማት የሚያመጡት ችግሮች

( እባክዎን ጠቃሚ መረጃ ስለሆነ ሼር በማድረግ ከአደጋ እንከላከል)

ብታምኑም ባታምኑም የጆሮ ማዳመጫ የመስማት ችሎታዎን ይጎዳል፡፡ የእንጨት መቁረጫ እና ሞተር ሳይክል 150 ዴስብል ድምፅ ያወጣሉ፡፡ የዚህን ያህል ድምፅ ደግሞ ከአንድ ሰዓት በአነሰ ጊዜ ውስጥ በጀሮዎ ላይ የመስማት ጉዳት ማድረስ ይጀምራል፡፡ በተመሳሳይም በከፍተኛ መጠን ሙዚቃ ወይም መዝሙር መስማት ከዚሁ ጋር የሚቀራረብ ድምፅ በማውጣት የጆሮን የመስማት አቅም እስከወዲያኛ ያዳክማል፡፡ በዚህ መሰረት በመስኩ ጥናት ያደረጉ የጤና ባለሙያዎች ቀጠሎ ያሉትን ማስጠንቀቂያዎች አውጥተዋል፡፡

1. የጆሮ ማዳመጫ ከ60 ደቂቃ በላይ በከፍተኛ መጠን (High Volume) መስማት የጆሮ የውስጠኛ ክፍል ኮቺሊያ(Cochlea) የያዛቸውን ቀጭን የጸጉር ሴሎች የድምፅ መልዕክቶችን ወደ አንጎል እንዳያስተላልፉ ያወድማቸዋል፡፡


2. የጆሮ ማዳመጫ አድርገው መንገድ የሚያቋርጡ

ብዙ ሰዎች የመኪና ወይም የባቡር ጥሩምባ ድምፅ መስማት ስለማይችሉ ለአደጋ ይጋለጣሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች በመላው ዓለም ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡

3. አዘውትረው የጆሮ ማዳመጫ የሚጠቀሙ ሰዎች በጀርሞች አማካኝነት ተላላፊ ለሆኑ የጆሮ ኢንፌክሽን ይጋለጣሉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የጆሮ ማዳመጫቸውን ከሌሎች ጋር ስለሚጋሩ ወይም ስለሚዋዋሱ ነው፡፡

4. የጆሮ ማዳመጫ ሽፋን የሆኑት ስፖንጆች ብዙ ጊዜ ስለማይጸዱ ወይም ስለማይታጠቡ ባክቴሪዎች በቀላሉ ይጎበኙዋቸዋል፡፡ ስለሆነም ቢያንስ በየሁለት ወሩ የጆሮ ማዳመጫ ስፖንጅ ይቀይሩ፡፡

5. ብዙዎቻችን የምንወደውን ሙዚቃ ሆነ መዝሙር ሌሎች እስኪሰሙን ድረስ መጠኑን ከፍ አድርገን የመስማት ልምድ አለን፡፡ እዚህ ላይ ልብ የማንለው ግን የሙዚቃው ከፍታ ከ100 ዴሲብል በላይ ሊዘል መቻሉ ነው፡፡ በዚህ ከፍተኛ ድምፅ የጆሮ ሴሎችና ታምቡር በጊዜ ሂደት በማዳከም የመስማት ዕክል ይፈጥራል፡፡

6. በመኪና ወይም በባቡር እየተጓዙ በጆሮ ማዳመጫ አድርጎ ሙዚቃ ወይም መዝሙር መስማት ሌላው እራስን ለጉዳት የሚዳርግ ተግባር ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የሚሰሙት ድምፅ ውጭ ካለው ድምፅ ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ ዴሲብል የሚረብሽ ድምፅ በመፍጠር የጆሮን የመስማት ችሎታ ይጎዳል፡፡

7. በከፍተኛ መጠን ያለው ድምፅ በጆሮ ማዳመጫ አድርጎ መስማት ቪርቲጎ (Vertigo) ለተባለ የራስ ማዞር በሽታ ይዳርጋል፡፡

8. የጆሮ ማዳመጫ አድርገው የሚያጠኑ ተማሪዎች አድርገው ከማያጠኑት ጋር ሲነፃጸር የአትኩሮት ማነስና በውጤታቸውም ቢሆን ዝቅተኛ መሆን እንደቻሉ የመስኩ ባለሙያዎች ጥናታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

9. የጆሮዎን የመስማት አቅም መቀነሱን ለማወቅም ከፍተኛ ድምፅ ያለው ሙዚቃ ወይም መዝሙር ከሰሙ በኃላ በጆሮ ውስጥ የደውል፣የማይቆም ኡኡ የሚልና ጭው የሚል ድምፅ ሊሰሙ ይችላሉ፡፡

10. ሙዚቃ ሲሰሙ ፣ቪዲዮ ጌም ሲጫወቱ እና ፊልሞችን ሲያዩ የድምፁ ከፍታ መጠን (Volume) በፍፁም ከ60 መብለጥ የለበትም፡፡ የሚሰሙት፣ የሚጫወቱት ወይም የሚያዩት የጊዜ መጠንም ከ60 ደቂቃ ባይበልጥ ይመከራል፡፡ አለም አቀፍ ሕጉ 60 በመቶ መጠን ለ60 ደቂቃ የሚል ነው፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ Share ያድርጉት::

በየጊዜው የምንለቃቸው የጤና መረጃዎች እንዲደርስዎ ፔጃችንን follow ያድርጉት::