August 1, 2019

ስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች ምርጥ ምግቦች


ምርምር እንደሚያሳየውና.............
በጉዳዩ ጥልቅ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች እንደሚነግሩን ከሆነ ስኳርን ክብደት በመቀነስ እና የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይቻላል።
የአኗኗር ዘይቤን መቀየር በቂ እንቅስቃሴ ማድረግና የሚበሉትን ምግብ መርጦ መብላት ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ምክንያቱም እንደምናውቀው ስኳር ከሰውነት ክብደትና ከምንበላው የምግብ አይነት ጋር በጣም ተያያዥነት አለው። በተለይ ስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች የሚበሉት ምግብ በጤና የመቆየታቸውንና በበሽታ መታወካቸውን ውሳኔ ይወስናል። አንዳንድ ምግቦች ስኳር ላለባቸው ሰዎች ምርጥ እና እንዲየውም 
ከአንዳንድ የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ጋር ሰውነት እራሱ ደም ውስጥ ይለውን የስኳር መጠን እንዲቆጣጠር ይረዳል ተብሎ
ይታሰባል።

እነሱም ምግቦች የሚከተሉት ናቸው።

1) ፖም:-

ፖም በጣም ብዙ የጤና ጥቅሞች አሉት ተብሎ ከተበየነለት ቆይቷል። ፖም በተፈጥሮው ዝቅተኛ ካሎሪ እና ከፍተኛ ፋይበር አለው። ፋይበር ደግሞ እንዳይርብ፣ መጥፎ ኮለስተሮልን ለመዋጋት እና ደም ውስጥ ያለው ስኳር ወደ ሁለቱ ጫፎች እንዳይወላውል ይረዳል።

በዛ ላይ ደግሞ ፖም ብዙ በሽታዎችን እንድንዋጋ የሚረዳንንና ለሰውነታችን በብዙ መልኩ የሚጠቅመንን anti oxident በበለጸገ መልኩ ይዟል።

2) አቮካዶ:-

አቮካዶ በ monounsaturated fat የበለጸገ ስለሆነ digestion ቀስ ብሎ እንዲካሄድና ከምግብ በኋላ ደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ጣሪያ እንዳይመታ ይቆጣጠራል።

እንዲየውም እንደ አቮካዶ አይነት ጥሩ fats ያሏቸው ምግቦች የደም የስኳር መጠን ጭራሽ ተመልሶ በተፈጥሮ ጤነኛ እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብሎ ይታሰባል።

3) ገብስ:-

ለምሳሌ ያህል በነጭ ሩዝ ፋንታ ገብስ መብላት ደም ውስጥ ያለውን ስኳር 70% ይቀንሳል። እሱ ብቻ ሳይሆን ገብስ በ ፋይበር የበለጸገ ስለሆነ የደም ስኳር መጠን ለሰዓታት ወይም ለረጅም ጊዜ ዝቅ ብሎ እንዲቆይ ይረዳል። ስለዚህ ገብስ ስኳር ላለበት እጅግ ምርጥ ምግብ ነው ተብሎ ይታወቃል።

4) ባቄላ/ቦለቄ እና ዘሮቹ:-

ቦለቄ/ባቄላ፣ አተር እና ሽምብራ አይነት ጥራጥሬዎች አንደኛ በፋይበር የበለጸጉ ናቸው። ሁለተኛ ደግሞ በ ፕሮቲንም የበለጸጉ ስለሆኑ የደም ስኳር መጠንን ዝቅ አድርጎ ለመጠበቅና እንዳይርብ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

5) እንቁላል(በመጠኑ):-

እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ከመሆኑም በላይ እንቁላል የፕሮቲኖች ወርቅ ተብሎ ተሰይሟል። በቀን አንድ ወይም ሁለት እንቁላል መብላት ኮለስትሮልንም ከፍ አያደርግም። ስለዚህ እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ስለሆነ ቶሎ እንዳንራብ ይረዳል።

6) አሳ:-

የስኳር በሽታ ዋነኛው መዘዝ የሚባለው የልብ በሽታ ነው። አሳ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቻ እንኳን መብላት ሰው በየትኛውም አይነት የልብ በሽታ የመያዙን እድል 40% ይቀንሳል።

7) የአበሻ አይብ:-

የአበሻ አይብ ከአብዛኞቹ አይቦች የሚለየው ቅቤው የውጣለት መሆኑ ነው። አይብ በካልሲዩምና በፕሮቲን የበለጸገ ነው። እንደ አይብ አይነት የወተት ምርቶችን በበቂ መጠቀም insulin resistance (የስኳር በሽታ ዋነኛው ችግር) ይዋጋል።

8) ለውዝ አና የለውዝ ዘሮች

ለውዝ በ monounsaturated fats የበለጸገና ከሰውነት ቶሎ የማያልቅ ምግብ ነው። እና እነዚህ ያሉት ባህሪይዎች ለስኳር እጅግ ተስማሚ ናቸው

9) የወይራ ዘይት:-

በአንዳንድ የጤና አኳያ ሲታይ የወይራ ዘይት ፈሳሽ ወርቅ ነው ተብሎ በብዙዎች ተሰይሟል። የወይራ ዘይት ከፍተኛ anti inflamatory ባህሪይ አለው። ይህ ደግሞ ስኳርን እና የልብ በሽታን የሚዋጋ ባህሪይ አለው ማለት ነው።

10) ቀይ ስጋ በመጠኑ:-

ቀይ ስጋ በ ፕሮቲን የበለጸገ እና ሰውነታችን ጮማ ከሚሆን በቂ የአካል እንቅስቃሴ ካደረግን በጡንቻ እንዲተካ ይረዳል።