August 1, 2019

የሱፍ ዘይት ጥቅም


ውድ የወይራ ተከታታዮች እንዴት ዋላችሁ ስለሱፍ ዘይት ጥቅም እነሆ 

የሱፍ ዘይት በቫይታሚን ኤ,ዲ እና ኢ የበለፀገ ነው፡፡ የሱፍ ዘይት የደም ዝውውርንና የልብ ጤናን ይጠብቃል፡፡ ይህም ሲባል ለልብ ህመም የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል፤ ተያያዥ ችግሮችንም ይቀርፋል፡፡ 
- የመገጣጠሚያ ህመሞችን ይከላከላል፡፡ ህመሙ ባጋጠመን ጊዜ ብንመገበውም በቶሎ ለማገገም ያግዘናል፡፡
- በሱፍ ዘይት ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኢ ለአስም የመጋለጥ እድላችንን ይቀንሰዋል፡፡ ለሳንባ እና ለቆዳ ካንሰር የመጋለጥ እድላችንን ይቀንሰዋል፡፡ የምግብ መፈጨት ሂደትን የተሳካ ያደርገዋል፡፡ በሽታ የመከላከል አቅማችንን ያሳድጋል፡፡ ከጤናማ ክብደት በታች የሆኑ ጨቅላዎችን ከኢንፌክሽን ይከላከልላቸዋል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ጤናማ የነርቭ ስራ ሂደት እንዲኖረን ያግዘናል፡፡ ፀጉራችን እንዳይሰባበር እና እንዳይሸብት ያደርጋል፡፡
ቆዳችንንም በፀሃይ አማካኝነት ከሚከሰት 
የካንሰር አይነት ይጠብቀዋል፡፡

ጤና ይብዛሎ!!