August 1, 2019

ብርቱካን የሚሰጠን 7 የጤና ጥቅም

ሰሞኑን ታዝባችሁ እንደሆን በመዲናችን አዲስ አበባ ብርቱካን በጣም በዝቷል፡፡ ሽንኩርትና ሙዝ፣ አልፎ አልፎም ፓፓያና ማንጎ በጋሪ እያዞሩ የሚሸጡት ጎረምሶች ሰሞኑን ብርቱካን በብርቱካን ሆነዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ፣ ለምን ስለብርቱካን የጤና ጥቅሞች ለወይራ ቤተሰቦች አንነግራቸውም ብለን አሰብን… ብርቱካን ለምን ለምን ይጠቅማል የሚለው እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡ በተረፈ “መልካም የብርቱካን ቀን ይሁንላችሁ” ብለናል - አሁኑኑ ሼር አድርጉት፡፡

1. ጤናማ ልብ እንዲኖረን የሚያደርገው ፖታሲየም መገኛ ነው።

2. ቫይታሚን ኤ በውስጡ ስላለው እይታችን የጠራና የተስተካከለ እንዲሆን ይረዳል በተጨማሪም የአይን ጤንነትን ይጠብቃል።

3. በፋይበር ክምችቱ ከፍተኛ ስለሆነ ጤናማ የምግብ ስልቀጣ እንዲኖረን ያግዛል።



4. በሽታ የመከላከል አቅምን የሚጨምረው ቫይታሚን ሲ ጥሩ መገኛ ነው።

5. ከፍተኛ የፎሌት መጠን ስላለው ሰውነታችን ቀይ የደም ሴሎችን እንዲያመርት ይረዳል።

6. ጤናማ እና ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን የሚያደርገው ካልሲየም በከፍተኛ ሁኔታ ይገኝበታል።

7. ቫይታሚን ቢ1 (Vitamin B1) በውስጡ ይገኛል ይህ ቫይታሚን ሃይል/ጉልበት በተለይ በጡንቻዎች እንዲመረት ይረዳል።

8. መረጃውን ከወደዱት ሼር አድርጉት፡፡

9. በዚህ አጋጣሚ ለወይራ ቤተሰቦች ቀጣዩን ቆየት ያለ ሙዚቃ ጋብዘናል፤

“ብርቱካን በልቼ፣ ሎሚ ሎሚ አገሳኝ
አንቺ እንደምን አለሽ እኔስ ልቤን ነሳኝ” - ይቅርታ ይደረግልን ግብዣው ሙዚቃ ለምትወዱ ብቻ ይሁንልን…