August 1, 2019

የእርድ ሻይ ክብደት ለመቀነስ የሚረዳው እንዴት ነው?


1. ፀረ-ኢንፌርሽን ባህሪያቶች አሉት
በሰውነትዎ ውስጥ ከመጠን በላይ መወፈር ወይም ከልክ ያለፈ ስብ መከማቸት ከፍተኛ ጉዳት አለው. እርድ የሆድ እብጠት እና የተዛመዱ የአየር ውጥረቶችን ለመቀነስ የሚያግዝ ፀረ-ኢንፌርሽን ቅመም ሲሆን ክብደት ለመቀነስ ጠቃሚ ነው.

2. አመጋገብ ስርዓትን ያስተካክላል
ጥሩ የምግብ መፍጫ ሥርዓት ክብደት ለመቀነስ 
ቁልፍ ነው. የእርድ ሻይ እንደ ጋዝ, የሆድ እብጠት እና የክብደት መለዋወጥን ለማስታገስ ይረዳል እንዲሁም ክብደትን ለመቀነስ የሚረዱ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን
ያሻሽላል.

3. የባይል ምርትን ያፋጥናል

በጨጓራ ውስጥ የሚገኘውን የባይል ምርት እንዲጨምር ያደርጋል፣ ይህ ስብ ለመቀነስ እና እንዲፈጭ የሚያግዝ ፈሳሽ ነው.

4. የደም ስኳር መጠን ይቆጣጠራል

የስኳር መጠን በመቆጣጠር ከመጠን በላይ ስብ በሰውነትዎ ውስጥ እንዳይቀመጥ ያደርጋል.

የእርድ ሻይ እንዴት ማዘጋጀት ይችላሉ :

- ግብዓቶች

እርድ
ዝንጅብል
ውሃ

- አሰራር

እርድ እና ዝንጅብል ውሃው ውስጥ በመጨመር ያንተክትኩት
እሳቱን አጥፍተው በማስቀመጥ እንዲቀዘቅዝ ያድርጉ.
ወደ ብርጭቆ ያጥልሉት