July 31, 2019

ለልጆች ፈጣን የአእምሮ እድገት የሚረዱ ምግቦችን እነሆ ብለናል

ለልጆች ፈጣን የአእምሮ እድገት የሚረዱ ምግቦች 
1. እርጎ 

፨ አእምሮ ላይ መልዕክት በተገቢው እንዲላክ እና እንዲቀበል ይረዳል፣ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ ይይዛል ይህ ደግሞ የአእምሮ ህብረ ህዋሶች እና መልእክት አስተላላፌዎች በተገቢው እንዲያድጉ

ይረዳል

2. አትክልቶች

፨ አትክልቶች አንቲ ኦክሲደንትነት አላቸው ይህ ደግሞ የአዕምሮ ህዋሶች ጤናማ እንዲሆኑ ይረዳል። ለምሳሌ እንደ ስኳር ድንች ፣ ዱባ ፣ ካሮት ያሉትን መስጠት ፣ እንደባሮ ሽንኩርት ፣ እስፒናች ፣ቆስጣ ያሉት ደግሞ በፎሌት የበለፀጉ ስለሆኑ ልጆችን ከመርሳት በሽታ ይከላከላሉ።

3. ብሮኮሊን
፨ ካንሰር ተከላካይነት ባህሪ አለው በተጨማሪም የነርቭ ስርዐት በተገቢው የተያያዘ እንዲሆን ያግዛል ።

4. አቮካዶ
፨ አስፈላጊ ቅባት (unsaturated fatty acid) ይይዛል ይህም በቂ ደም ወደ ጭንቅላት እንዲዘዋወር ይረዳል ፤ ኦሊክ አሲድ በመያዙ ምክንያት ማይሊን የተባለውን የአዕምሮ ክፍል ከመጥፎ ነገር ይከላከለዋል( ማይሊን በሰዐት በ200 ማይል ፍጥነት መልዕክት እንዲተላለፍ ያደርጋል) ፤ በቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ መሆኑ ልጆች በግፌት የመያዝ እድላቸውን ይቀንሳል ።

5. አሳ
፨ በኦሜጋ 3 የበለፀጉ ናቸው ( ለአዕምሮ እድገት ይረዳሉ)

6. እንቁላል
፨ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል ለምሳሌ ኦሜጋ 3፣ ዚንክ፣ ኮሊን( አሴታይል ኮሊን እንዲመረት ይሚረዳ ሲሆን የማስታወስ ችሎታን ለማዳበር ያግዛል)

7. የተፈጨ አጃ
፨ በተለይ ለቁርስ ብንመግባቸው ጥሩ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖራቸው ይረዳል በተጨማሪም በቫይታሚን ኢ፣ ዚንክ ፣ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ ነው። ከፍተኛ ፉይበርነት ስላለው ሀይልን እንዲያገኙም ያደርጋል ።