July 31, 2019

የአናናስ 3 አስደናቂ ጥቅሞች



አናናስ በማእድናት እና በቫይታሚን የጎለበተ በመሆኑ ለሰውነታችን እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት። በውስጡም ቲያሚን፣ ቫይታሚን ቢ6፣ ኮፐር፣ ቫይታሚን ሲ፣ ማንጋኒዝ እና ሌሎችንም ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ነው።

• ከፍተኛ የሆነ የማቃጠል ስሜትን ይቀንሳል ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የማቃጠል ስሜት ለብዙ በሽታዎች ካንሰርን ጨምሮ ለልብ ህመም፣ ለታይፕ 2 የሥኳር ህመም (Type 2 diabetes)፣ ለመገጣጠሚያ ህመምና የመሳሰሉት ያጋልጣል። ሆኖም አናናስ ረጅም የማቃጠል ስሜትን በመቀነስ በማቃጠል ምክንያት የሚከሰቱን በሽታዎች ማስቀረት ይቻላል።

• የአጥንት ጤንነት ይጠብቃል
አናናስ ለጠንካራ አጥንትና ለተያያዥ ሴሎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለውን

ማንጋናይዝ የተሰኘውን ማዕድን ይይዛል። አናናስ በቀን መጠቀም ከሚገባን 75% ያህሉን አካቷል።

• በሽታን የመከላከል አቅምን ያጠነክራል

አናናስ በቀን መጠቀም የሚገባንን 50% ቫይታሚን የያዘ ነው። ይህ ቫይታሚን በውስጡ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ጥቃቅን ነገሮችን የመጨመርና ሴሎችን ከጉዳት የመጠበቅ አቅም ያለውን ኣንቲ ኦክሲዳንት ይዟል።

#ማስጠንቀቂያ - የአናናስን ተፈጥሮአዊ በረከቶቹን ለማጣጣም በፋብሪካ ያልተቀነባበረውን እና ከማሳ የተሰበሰበውን መመገብ ይኖርብናል። በፋብሪካ የተቀነባበረው የስኳር መጠኑ ከፍ ስለሚል ጠቀሜታው እንብዛም ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት በተደጋጋሚ አናናስ መመገብ የጤና ደረጃን የተሻለ ከማድረጉም ባሻገር ከበርካታ አይነት በሽታዎችም ይከላከልልናል።

#ሌላ_ማስጠንቀቂያ - ሼር ማድረግዎን አይርሱ