July 30, 2019

የእርጎ ጠቀሜታ በከፊል


እርጎ ለጤና ከሚሰጠው ጥቅም በዘለለ ለውበት እና ለፅዳት ተመራጭ መሆኑንስ ያውቃሉ?

እርጎ እጅግ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን፥ በዋናነትም ለምግብ መፈጨት ሂደት ፣ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጎልበት፣ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ፣ ለአጥንት ጥንካሬ ወዘተ ወሳኝ የምግብ አይነት ነው።

1.እርጎ ማራኪ የፊት ቆዳ እንዲኖረን ይረዳል፣

እርጎ በተፈጥሮ የያዘው ላክቲክ አሲድ የሞቱ ህዋሶችን ከቆዳችን


የላይኛው ክፍል ላይ በማስወገድ በአዳዲስ ህዋሶች እንዲተኩ ያደርጋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፊት ላይ የሚስተዋሉ አላስፈላጊ እና ጥቋቁር ምልክቶች ፣ በተለምዶ

ጭርት የምንለውን እና የቆዳ መበለዝን ሳይቀር ለማስወገድ ተመራጭ ነው።

ታዲያ እርጎውን በውጤታማ መንገድ ለፊታችን ውበት ለማዘጋጀት የሚከተለውን መመሪያ መተግበር ያሻል ፦

√ አንድ ኩባያ በደንብ የረጋ እርጎ


√ ሁለት ወይም ሶስት የሾርባ ማንኪያ ማር

√ ሁለት ወይም ሶስት የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት

√ እርጎውን ከማሩ እና የወይራ ዘይቱ ጋር በሚገባ ካዋሃዱ
በኋላ ፊትዎን በደንብ ይቀቡት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ድረስ ካቆዩት በኋላ ለብ ባለ ውሃ ይለቃለቁት ።

ውበታችን በእጃችን ስለሆነ ሌሎች መዋቢያ ብለን ከምናወጣው ነገር በቀላል ዘዴ በቤት ውስጥ መጠበቅ እንችላለን