July 31, 2019

ሆድ ሲቆጣ መመገብ ያለብዎ 5 ምግቦች



ሆድ ሲቆጣ መመገብ ያለብዎ 5 ምግቦች

ሆድ ህመም ከተለያዩ የህመም ምልክቶች ጋር አብሮ ሊፈጠር ይችላል ። ማቅለሽለሽ ፣ የሆድ መነፋት፣ ተቅማጥ ወዘተ። በዚህ ግዜ ቀለል ያሉ ምግቦችን መመገብ የሚመከር ሲሆን አንዳንድ ምግቦች ለሆድ ጤና የሚሰጡት ጥቅም የጎላ ነው።

ሙዝ

ማራቶን ሯጮች ሙዝን የሚያዘወትሩበት ምክንያት አለ ። ሙዝ በቀላሉ የሚፈጭ ምግብ ሲሆን ሆድ በቀላሉ እንዲቆጣ አያደርግም ። ሙዝ በተለይ በውስጡ ፔክቲን የሚባል ለሆድ ማብላላት የሚረዳ ንጥረ ነገር ይይዛል።

ፓፓያ

ፓፓያ የሆድ መፍጨትን ብቃት የሚያግዝ ምግብ ነው። ከሆድ ድርቀትም ይከላከላል። በውስጡ የያዛቸው ፓፓይን እና ቻይሞፓፒን የሚባሉ ኢንዛይሞች ፕሮቲኖች እንዲዋሃዱ በማድረግ ይታወቃሉ ። ሆድ ጤነኛ

የአሲዳማ ይዘት እንዲኖረው ያደርጋሉ ።

ነጭ ሩዝ

ሆድ በተቆጣበት ግዜ ነጭ ሩዝ፣ ቶስት እና የተቀቀለ ድንች መመገብ ይመከራል። እነዚህ ምግቦች ሆድ ላይ ጫና አይፈጥሩም። ከዛም አልፎ ተቅማጥን በመጠኑም ቢሆን ያስታግሳሉ ። ፈሳሽ የመምጠጥ ችሎታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ሰገራ ደረቅ እንዲል ያደርጋሉ ።

ዝንጅብል

ዝንጅብል የማቅለሽለሽ ስሜትን በማስታገስ እና የሆድ መፍጨት ችሎታን በማገዝ ይታወቃል። ከሆድ መመረዝ በኋላ ዝንጅብል እንድንበላ ይመራል።

አረንጓዴ ሻይ

ፔፐርሜንት እና ካሞሚል ሻዮች የሆድ ህመምን በማስታገስ ይታወቃሉ። ፔፐርሜንት ሻይ ለሆድ ከሚሰጠው ጥቅም አልፎ የቆሰለ ጉሮሮን ለማከም ይረዳል። ካሞሚል ሻይም ቢሆን የሆድ ህመምን በማስታገስ ይታወቃል ።

ጤነኛ ምግቦችን በመመገብ ጤናችንን እንጠብቅ