July 31, 2019

የፓፓያ የውበት ጥቅሞች

የፊቶን ውበት እንዴት በቀላሉ መጠበቅ እንደሚችሉ ያውቃሉ ? እንጊዲያውስ ዛሬ በቀላሉ የፊቶን ውበት እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ እንነግሮታለን ይከታተሉን

የፓፓያ የውበት ጥቅሞች 

1 የፊት ቆዳን ለማሳመር 

አዘገጃጀት ፡ - 2 የሾርባ ማንኪያ ፓፓያ ጁስ ፣ 1 የሻይ ማንኪያ ማር አንድ ላይ አድርጎ መቀላቀል ውህዱን ፊት ላይ ተቀብቶ 30- 45 ደቂቃ አቆይቶ በቀዝቃዛው መታጠብ


2 ጥርት ላለ የፊት ቆዳ ፡- ፊታችን ላይ ያለ ጥቁር ነጥቦችን ወይንም በብጉር ምክንያት የሚከሰት ጠባሳዎችን ለማጥፋት ይረዳል

አዘገጃጀት ፡- 2 የሾርባ ማንኪያ ፓፓያ ጁስ ማዘጋጀት ጁሱን ንፁህ ፊት ላይ መቀባት ከዚያ እስኪደርቅ ድረስ ጠብቀው መታጠብ

3 የፊት ቆዳ እንዳይሸበሸብ ፡-

አዘገጃጀት ፡ - ፓፓያን መላጥ ፣ የፓፓያውን ልጣጭ ( በውስጥ በኩል ያለውን ) ፊታችንን መቀባት በልጣጩ ፊታችንን ቀስብለን ማሸት ከዚያ ከ 15 ደቂቃ በኋላ ፊታችንን በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ

ከላይ የጠቀስናቸውን ውህዶች ፊታችን እንዲያበራና እንዲለሰልስ በማድረግ የፊታችንን የቆዳ ውበት ይጠብቅልናል ፡፡