July 31, 2019

7 ካንሰር ተከላካይ ምግቦች

7 ካንሰር ተከላካይ ምግቦች


ሁሉም ምግብ ለጤና ተስማሚ ነው ተብሎ የተቀመጠ ነገር የለም። እንደውም አንዳንዶቹ ለሰዎች የመጥፊያ ያህል የሚቆጠሩ በሆኑበት ዓለም ለዘለቄታው ከጤናችን ጋር የማይጋጩትን ምግቦች የመምረጥ ግዴታ ውስጥ መግባታችን ተጨማሪ ስራ ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም ሲሉ የስነ ምግብ ተመራማሪዎች ያስገነዝባሉ፡፡ ለጤና ጠንቅነታቸው አሳሳቢ የሚባሉ ምግቦች የመኖራቸውን ያህል ታዲያ በሽታን በመዋጋት የተመሰገኑ ምግቦች መኖራቸውን መዘንጋት የለብንም፡፡ ለዚህ ንፅፅር ባለሙያዎች የዳብል በርገርን ተደራራቢ የጤና ጠንቅነትና አረንጓዴ ጎመን የሚለግሰንን ሌላ ተደራራቢ የጤና ጥቅምን በምሳሌነት ይጠቀማሉ፡፡ ለዛሬ በካንሰር ተከላካይነታቸው በምርምር ውጤቶች ጭምር የተረጋገጠላቸውን ምግቦችን እንመለከታለን፡፡
በእርግጥ አንድ ምግብ ለህክምና ጭምር ፈተና የሆነውን ካንሰርን ሙሉ ለሙሉ ሊያስቆም ባይችልም ሰውነታችን ካንሰርን እንዲዋጋ ከፍተኛ አቅም በመፍጠር ረገድ ግን
የማይተካ ሚና አላቸው፡፡ በቅድሚያ ተመራማሪዎች የተቀነባበረ ሥጋን፣ ጨው የበዛባቸውን ምግቦችና የስኳር ክምችታቸው ከፍተኛ የሆነን መጠጦች ከአመጋገብ ዝርዝራችን ውስጥ እንድናርቅ ይመክሩናል፡፡
የአሜሪካ የካንሰር የምርምር ኢንስቲቲዩት ከተክል የሚገኙት በተለይ አረንጓዴ ጎመን፣ እንጀራና ነጭ ሽንኩርት ከፍተኛ የካንሰር ተከላካይነት ባህሪ የታየባቸው እንደሆነ በጥናቱ አስረድቷል፡፡
እነዚህ ተክሎች እጅግ ዝቅተኛ መጠን ያለው ካሎሪ በውስጣቸው ሲገኝባቸው ለካንሰር ተጋላጭነታችንን የሚቀንሱልን ሳይኬሚካል እና አንቲ ኦክዲዳነቶችን በውስጣቸው የያዙ ናቸው፡፡

1.
ነጭ ሽንኩርት፡- ነጭ ሽንኩርት በአፋችን በማንፈልገው መዓዛ ሊቀይር የሚችል ቢሆንም ትልቅ የጤና ዋስትና ነው፡፡ በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኘው የመአዛ ድብልቅ በሰውነታችን ውስጥ የካንሰር አማጪ ንጥረ ነገሮች መሰረት እንዳይዙ ነጭ ሽንኩርት አልኮል እና ትውልድ ካንሰር ጋር የቀጥታ ግንኙነት ካለው ኤችፕሎሪ ባክቴሪያ ጋር እንዲሁ ይፋለማል፡፡ በትልቁ አንጀት ላይ ሊፈጠር የሚችለውን የካንሰር አደጋም እንዲሁ ይቀንሳል፡፡

ነጭ ሽንኩርታችንን በጥሩ ሁኔታ ለመጠቀም ካጠብን በኋላ ወደ ማብሰል ከመግባታችን በፊት 15 እና 20 ደቂቃ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ ይሄ አካሄድ በውስጡ ያሉ ኢንዛይሞች እንዲነቃቁ ሲያደርግ ነጭ ሽንኩርቱ በውስጡ ያከማቸውን ሰልፈር እንዲያስወግድ ዕድል እንሰጠዋለን፡፡

2.
አረንጓዴ ጎመን፡- (አሳይቶ ኬሚካል መገኛ) አረንጓዴ ጎመንን ጨምሮ ጥቅል ጎመን፣ አበባ ጎመን እና ሌሎች የጎመን ዘሮች ሳይ የኬሚካልስ እና በሊኮ ሲኖሌትስ የተሰኙ ማዕድናትን በውስጣቸው ይዘዋል በዚህም ምክንያት የበሽታ የመከላከያ ኢንዛይሞችን የማመንጨት አቅም እንዲኖራቸው ሆኗል፡፡

3.
ቲማቲም፡- (የፕሮስቴት ካንሰር መከላከያ መሳሪያ) ቀዩ ቲማቲም የፕሮስቴት ካንሰርን (የወንድ የመራቢያ አካልን የሚያጠቃ) በመከላከል ረገድ የተመሰከረለት ነው፡፡

ከቲማቲም የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ በተቻለ መጠን እሳት የነካውን ወይም የተቀነባበረውን ቲማቲም እንድንመገብ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ይሄ ታዲያ በጁስ መልክ የሚዘጋጀውን እና ለፒዛ የሚቀርበውን ቲማቲም ሶስ ይጨምራል፡፡ የተቀነባበረው ቲማቲም ካንሰርን የሚከላከሉ ውህዶች የበለጠ የተነቃቁ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
4.
ስፒናች (ጎመን)- ስፒናች ለዓይን ጤንነት እጅግ ጠቃሚ የሚባለውን ሎቴን አንቲ ኦክሲዳንት በውስጡ ይይዛል፡፡ ተመራማሪዎች ካንሰርን በቀላሉ ስለመዋጋቱ ማረጋገጫ ባይሰጡም እንደሌሎቹ አቻ ተክሎች ሁሉ የካንሰርን የመከላከል አቅም ለሰውነታችን እንደሚሰጥ እርግጥ ነው፡፡ የስፒናች ቅጠል ለሆድ እንዲሁም ለአፍ የጉሮሮ ወይም የምግብ ቧንቧ የሚያጠቃውን የካንሰር አይነት እንደሚከላከል ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ስፒናችን አዘውትረው በሚመገቡ 490 ሰዎች ላይ የተሰራ ጥናት አፍና የጉሮሮ ካንሰር የመጠቃት ዕድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን ነው ጥናቱ ያሳየው፡፡

5.
ካሮት፡- በቀላሉ የሚወደድ አትክልት ነው፡፡ ካሮት በሽታን በሚዋጉ ንጥረ ነገሮች የተከበበ ነው፡፡ ተክሉ የካንሰር ሴሎችን የማውደም እና ዕድገታቸውን የመግታት አቅም ያለውን ካሮቲን የተሰኘ አንቲ ኦክሲደንት (Antioxidant) መገኛም ነው፡፡ በተመሳሳይ እንደ ጎመኖቹ ሁሉ ካሮትም ቪታሚኖችን እና አንዳንድ ኬሚካሎችን የማመንጨት አቅሙን በመጠቀም በአፍ፣ በጉሮሮና በሆድ አካባቢ ሊከሰት የሚችልን ካንሰር በብቃት ይከላከልልናል፡፡ እንደ ተማሪዎች መመሪያ ካሮትን ከአሁን በኋላ ስንመገብ ለኩረጃ የሚረዳንን የዓይናችንን ጥራት ለማሳደግ ብቻ እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ካሮት በተጨማሪም የማህፀን በር ካንሰርንም የመከላከል ከፍተኛ አቅም አለው፡፡

የበሰለው ካሮት በጥሬው ከምንጠቀመው በተሻለ መልኩ በሽታ ተከላካይ አንቲኦክሲዳንቶችን ያመነጫል ይላሉ ተመራማሪዎች፡፡ በግብርና እና የምግብ ኬሚከስትሪ መፅሔቶች መመሪያ መሰረት ካሮታችንን ከቀቀልን እና የመብሰል ሂደቱን ሲጨርስ ብቻ ነው እንድንቆርጠው የሚያዙን፡፡ ይሄም ጣፋጭነቱን ከማሳደጉም በላይ ካሮቱ ንጥረ ነገሮችን ከውስጡ እንዳያጣ ያደርጋል፡፡