July 31, 2019

የጋንግሪን በሽታ እንዴትና በምን ይከሰታል?

የጋንግሪን በሽታ እንዴትና በምን ይከሰታል?

ጋንግሪን ማለትአንድ የሰውነት ክፍል ደም አጥሮት ምግብና ኦክስጅን አልደርሰው ብሎ ከሙሉ አካላችን ተለይቶ የተወሰነ የሰውነታችን ክፍል እየሞተ ወይም በድን እየሆነ መምጣት ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- በተለያዩ አደጋዎችና ሌሎች ምክንያቶች በአካላችን የተለያዩ ክፍሎች የደም ዝውውር ቢቋረጥ፣ የተቋረጠበት የሰውነት ክፍል ጋንግሪን ይፈጥራል፡፡
መንስኤዎቹ
የልብ ችግር ያለባቸው ሰዎች ደም ይረጋና ከልብ ወደ ደም ስሮች ይሄዳል፤በጣም ትንሽም ብትሆን የረጋች ደም የደም
መተላለፊያ ትቦዎችን ትዘጋለች፤ በዚህ ጊዜ ይህ ደም ይመግበው የነበረው የሰውነት ክፍል
• ምንም ማግኘት ስለማይችል ጋንግሪን ይፈጥራል፡፡
• የበደም ስር ጥበት

• ለረጅም ጊዜ የስኳር ሕመም የገጠማቸው ሰዎች
• የደም ግፊት ችግር ያለባቸው እንዲሁም ከፍተኛ

የደም ቅባት ያለባቸው ሕሙማን የደም ስራቸው ሊጠብ ይችላል፡፡
• የቁስል ማመርቀዝ ወይም ኢንፌክሽን ከተፈጠረ
• እንደ እጅና እግር ያሉ አካላትንም ደም እንዳይዘዋወር አጥብቀን ለረዥም ሰዓት ካሰርናቸው ጋንግሪን ያስከትላል፡፡
በሽታው የሚከሰተው አብዛኛውን ጊዜ በስኳር፣ በልብ እንዲሁም በደም ግፊት ሕሙማን ላይ
በመሆኑ እነኝህ በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች የተለየ ክትትል ማድረግ አለባቸው፤ በተለይ ማንኛውንም ቁስለት ችላ ማለት የለባቸውም፡፡
ሕክምናው
ጋንግሪን የሞተ የአካል ክፍል በመሆኑ የተጠቃውን በድን አካል ማስወገድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በዚህ ምርጫ ደስተኞች አይሆኑም፤ ሐኪሞችንም ለመቁረጥ ይፈጥናሉ የሚል አስተያየት ይሰጣሉ፤ ሌሎች አማራጮች ካሉ በማለትም መፍትሔ በማፈላለግ ጊዜ ይሰጣሉ፤ ይህ ሁኔታም በሽታው ስር እንዲሰድ ክፍተት ይፈጥራል፤ በጋንግሪንየሚሰጡትን የመዳን ውሳኔ በጊዜ መቀበል ህይወትን ሊያድን ይችላል፡፡
ሌላው ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ህመሞችን ልክ እንደስኳር ደም ግፊት፡የደም መርጋት ካሉ ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡