July 30, 2019

ከአብሽ (Fenugreek) የምናገኛቸው የጤና በረከቶች

አብሽ ከሺህ ዓመታት በፊት በቻይና አገር የቆዳና ሌሎች በሽታዎችን ለመፈወስ በአማራጭ ሕክምና ወይም በባህላዊ ሕክምና ረገድ ሲገለገሉበት ቆይተዋል፡፡በቅርቡ ደግሞ በቤት ውስጥ በማጣፋጫ ቅመምነት(Spice) እና በተጨማሪ የምግብ ግብዓት(Supplementary Food) ሆኖ ከማገልገሉ በተጨማሪ በአንዳንድ የሳሙናና የሻምፖዎች አይነቶች ሁሉ ሳይቀር በመግባት ጥቅም በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

አብሽ ከፍተኛ ካሎሪን በውስጡ ከመያዙ በተጨማሪ የተለያዩ የምግብ ንጥረ ነገሮችን በስፋት የያዘ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ጥሩ መጠን ያለው ፋይበር፣ ፕሮቲን፣ ቅባት፣ ካርብስ፣ ብረት፣ ማንጋኒዝና ማግኒዚየም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለመሆኑ ከአብሽ የምናገኛቸው የጤና በረከቶች ምንድን ናቸው?

1. ልጅ ከወለዱ በኃላ በቂ የጡት ወተት እጥረት ላለባቸው እናቶች አብሽ መጠጣት የጡት ወተት ምርትን በመጨመር ወደር ያልተገኘለት ነው፡፡ ለህፃኑም ክብደት መጨምር ከፍተኛ አስተዋፆ ይኖረዋል፡፡

2. የወንድ ልጅ የዘር ሆርሞን መጠን ከመጨመር ባሻገር ወንዶች የተሻለና ጠንካራ የወሲብ ብቃት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡
3. አብሽ የኢንሱሊን ተግባርን በማሻሻል አይነት 1 እና 2 የስኳር በሽታን ከመቆጣጠሩ በተጨማሪ የደም ስኳር መጠንን ይቀንሳል፡፡
4. መጥፎ ደም ቅባት ወይም ኮሌስትሮል መጠንን በእጅጉ

ይቀንሳል፡፡
5. የምግብ ፍላጎታችንን ይቆጣጠራል፡፡በዚህም በአጠቃላይ የምንወስደውን የቅባት መጠን ዝቅ እንዲል ያደርጋል፡፡
6. የፀረ-አሲድ ሕክምና በማድረግ የቃር ምልክቶችን ይቀንሳል፡፡
7. ፀረ-ብግነት (anti-inflammatory) በመሆን ያገለግላል፡፡
8. ለልብ ሕመም፣ለወር አበባና ለምግብ መፈጨት ችግሮች መድኃኒት ነው፡፡
9. ለጉሮሮ ቁስልና ለሆድ ድርቀት መፍትሔ ነው፡፡
10. አብሽ ለቆዳ ልስላሴና ለተለያዩ የቆዳና የፀጉር የጤና ችግሮች መፍትሔ የሚሰጥ መሆኑን የተለያዩ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡
ይህ ሁሉ ጥቅም ያለው አብሽ መለስተኛ የሆነ የጎንዮሽ ውጤት (side effect) እንዳለው በመጠኑ ተዘግቧል፡፡ በተለይ የተለየ የሰውነት ሽታ ማምጣቱ፣ ሕመምተኛ ሰዎች ከወሰዱት አልፎ አልፎ ሊያስቀምጣቸውና የምግብ ያለመፈጨት ችግር ሊያጋጥማቸው እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡

መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ!

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው!