July 30, 2019

የ ወፍ በሽታ (ጉበት)

ዛሬ በተደጋጋሚ ስለተነሳ የወፍ በሽታ ምልክቶች እንዲሁም መፍትሔ በሰፊው የምናይ ይሆናል።
በተለይ ብዙ ጊዜ ላልሆነው የወፍ በሽታ የማዳን ኃይሉ ከፍተኛ ነው።
ለጉበታችን ጤንነት እንድንጨነቅ እና እንድንጠነቀቅለት የሚያደርግ በርካታ የሆኑ ተግባሮችን/ስራዎችን ጉበታችን በመወጣት ይጠቅማል፡፡ የሚከተሉት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጉበት ጉዳት ምልክቶች ናቸው፦

የቆዳ ቀለም ለው

በአይናችን ልናየው የምንችለው የጉበት ጉዳት/በሽታ ምልክት የቆዳ ቀለም ለውጥ ነው፡፡ የቆዳዎ ቀለም ቢጫ ወይም የገረጣ/የፈዘዘ እየሆነ ከመጣ ጉበትዎ በትክክል ስራውን እየተወጣ አይደለምማለት ነው ስለዚህ እርዳታ ያስፈልግዎታል ማለት ነው፡፡ ይህ የቆዳችን ቀለም ወደ ቢጫነት መቀየር ዋነኛ ምክንያት ጉበታችን መርዛማ ነገር(ቶክሲን) ስለማይለቅ ሲሆን የዚህ መርዛማ ነገር አለመለቀቅ ቢሊሩቢን በቆዳዎች አካባቢ እንዲጠራቀምያደርገዋል፡፡

የሆድ ህመም

ጉበታችን የሚገኝው በጎድን አጥንታችን አካባቢ ሲሆን የጉበታችን ጤናማ አለመሆን በሆዳችን እና በጎድን አጥንታችን አካባቢ ከፍተኛ የህመም ስሜት
ይፈጥራል፡፡

በተደጋጋሚ ማግሳት

በሆድ/አንጀት በአየር መነፋት ምክንያት በተደጋጋሚ በግሳት የሚሰቃዩ ከሆነ ጉበታችን ምግብን ለመፍጨት የሚሆን ኢንዛይም ማምረት ተስኖታል ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም የምግብ መፍጨት ስርዓታችን በጉበት ችግር ምክንያት ይታወካል፡፡

የድካም ስሜት መሰማት

ጉበት ምግብን በሚሰባብርበት/እንዲፈጭ በሚያደርግበት ጊዜ በየቀኑ ስራችንን ለመስራት የሚጠቅም ሃይል/ጉልበት እንድናገኝ ያደርጋል፡፡ በቀላሉ የምንደክም ከሆነ የጉልበት ማጣት ምልክት ነው ይህም ጉበታችን ሥራውን በትክክል አለመወጣቱን ያሳያል፡፡

የሽንት ቀለም መለወጥ

ጉበታችን መጎዳት በሚጀምርበት ጊዜ የሽንታችን ቀለም ጠቆር ወዳለ ቢጫ ይቀየራል አንደንዴም ወደ ደም ቀለም ሊወስደው ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህ የቀለም ለውጥ ከፈሳሽ እጥረት እንደመጣ ያስባሉ በቂ ውሃ ጠጥተው ይህ የቀለም ለውጥ ከተከሰተ የኩላሊት ጤና ታውኳል ማለት ነው፡፡

ቆዳን ማሳከክ

የጉበት በሽታ ማሳያ ከሆኑት አንዱ የቆዳ ማሳከክ ነው፡፡ በቆዳዎ ላይ የሚያሳክክ ቦታ ካለ እና ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ከመጣ የጉበት ችግር ምልክት ነው፡፡

ማቅለሽለሽ

የምግብ አለመፈጨት እና የአሲድ አለመመጣጠን የጉበት ጉዳት ምልክቶች ናቸው፡፡ የምግብ አለመፈጨት እና ማቅለሽለሽ የአመጋገብ ሁኔታችንን በመቀየር የማይስተካከል ከሆነ የጉበት ችግር ምልክት ነው፡፡ እየተባባሰ ሲሄድ ማስታወክ ደረጋ ላይ ይደርሳል፡፡

የክብደት መቀነስ

ድንገተኛ የሆነ የክብደት መቀነስ እንደ ጉበት ችግር ሊታይ ይችላል፡፡ ሳይፈልጉ ክብደት የሚቀንሱ ከሆነ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሊሆን ይችላል ይህም የሚሆነው ጉበታችን ደካማ ስለሚሆን ሲሆን ቀጭን እና የተጎዳ ሰው እንድንሆን ያደርገናል፡፡

ፈሳሽን መያዝ

በተላያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ፈሳሾች መቋጠር/መያዝ በተለይ በእግር አካባቢ የደካማ ጉበት ምልክት ነው፡፡
ይህ ሁኔታ ኢዴማ(Edema) ይባላል እብጠት ይመስላል፡፡ ይህ እብጠት በጉልነት፣ እጅ አና እግር ጣቶች አካባቢ ይከሰታል፡፡ ያበጡትን ጣቶች ስንጫናቸው ጊዜ ለጥቂት ሰከንዶች ወደውስጥ ገብተው/ጎድጉደው ይቀራሉ፡፡

የአይነ ምድር ቀለም መቀየር
የአይነ ምድር ቀለም መቀየር አንድ የጉበት ችግር ምልክት ነው፡፡ ትንሽ ደም ከአይነ ምድር ጋር ተቀላቅሎ የሚወጣ ከሆነ በፍትነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ አለብን፡፡ ሌላው ከአይነምድር ጋር የተያያዘ የጉበት ችግር ምልክት የሆድ ድርቀት ነው፡፡

እነዚህ ምልክቶች በሳይንሱ ዓለም እና በባህሉ ዓለም የተጠኑ እና የወፍ በሽታ ወይም ጉበት ምልክቶች ናቸው።

የወፍ በሽታ ወይንም ጉበት መፍትሔ ብስር እንደሚከተለው አስቀምጨዋለሁ።

የወፍ በሽታ መፍትሔ

፨የምድር እንቧይ፨

የምድር እንቧይ በምስሉ የሚታየው ምድር ለምድር የሚበቅል በብዛት በክረምት ወቅት የሚበቅል ቅጠሉ እና ፍሬው ሸካራ የሆነ ዕጽ ነው።

የምድር እንቧይ ሥር በአውራ ጣታችን ልክ በመቁረጥ ውፍሩቱም በአውራ ጣታችን መጠን በመገመት እንቆርጥ እና!

በውኃ በደንብ አጥበን በንጹህ ቦታ በእርጥቡ አልሞ መጨቅጨቅ ከዛ በኃላ የላመው የምድር እንቧይ ሥር በአንድ ሾርባ ማንኪያ ንጹህ ነጭ ማር በትንሽ ውኃ አድርገን በማሸት በማጥለያ አጥለን በአንድ ሲኒ እስከ አፏ ሳንሞላ እርከኗ ድረስ ለክተን ጧት በባዶ ሆድ አንድ መውሰድ።

ይህ ክንውን አንድ አንድ ቀን እየዘለልን ለ 3 ቀን እንውሰድ ብዙ ጊዜ ላልሆነው የወፍ በሽታ በፍጥነት ያድነዋል የቆየ ከሆነም ቀስ እያለ ይጠፋል።

ይህ መፍትሔ በምንወስድበት ሰዓት ትንሽ ወደታች የማለት ባህሪ አለው።
የከበዳችሁ እንደሆነ ትኩስ ነገር ወይም ትኩስ ቡና ብትጠጡበት ወደታች ማለቱ ያቆምላችኃል።

ይህ መፍትሔ በተለያዩ የጥበብ ባለቤቶች ይሰጣል። ግን በይፋ አይወጣም ይህ የእጽዋት ጥበብ የማትጠቀሙበት የተለያያችሁ የጥበብ ባለቤቶች እና የባህል ሐኪሞችም ሊጠቅማችሁ ይችላል ብየ እገምታለሁ ምክንያቱም አድካሚ ስላልሆነ።

መፍትሔውን ተጠቅማችሁ የምታውቁ አልያም አስጠቅማችሁ ያረጋገጣችሁም ከቻላችሁ በ comment ስር እውነታውን ግለጡ።

እንዲሁም በተለይ በገጠር አከባቢ ይህ በሽታ ይበዛል እና ይህ መልእክት አይተው በመጠቀም ከህመማቸው ይፈወሱ ዘንድ!
ሼር ሼር ሼር በማድረግ መፍትሔውን እናዳርስ።