July 31, 2019

የበቆሎ የጤና በረከቶች


ከአስር ሺህ ዓመታት በፊት ከደቡብ ሜክሲኮ ለዓለም የተበረከተው በቆሎ አገራችንን ጨምሮ በመላው ዓለም ተወዳጅነትን ያተረፍ የምግብ አይነት ነው፡፡ በቆሎ በእኛ አገር እሸቱ ተቀቅሎ፣ተጠብሶና ተፈልፍሎ ተቆልቶ ይበላል፡፡ ፍሬው ሲደርቅ ደግሞ ተጨምቆ ዘይት ከመሆን አልፎ ዱቄቱ ለዳቦ፣ለገንፎና ለሌሎች የምግብ አይነቶች መስሪያነት በግብዓትነት ይውላል፡፡ ለመሆኑ ከጤናችን አንፃር በቆሎ በሳይንስ የተረጋገጡ ምን ጠቀሜታዎች አሉት?

1. የኪንታሮት በሽታን ይከላከላል፡-ከፍተኛ የፋይበር ይዘት ስላለው የሆድ ድርቀትን በማስወገድ የኪንታሮት በሽታን ይከላከላል፡፡
2. እድገትን ያፋጥናል፡- የቫይታሚን ቢ ንጥረነገሮች የሆኑትን ቲያሚና ኒያሲን ስላላው ለአጠቃላይ የሰውነት ዕድገትን ያበረታታል፡፡

3. ክብደት ለመጨመር ይረዳል፡- ክብደቶ ከሚጠበቀው ኪሎ በታች ነው? እንግዲያውስ ከፍተኛ የካሎሪን መጠን ያለውን በቆሎ ቢያዘወትሩ በፍጥነት ክብደት ለመጨመር

ይረዳዎታል፡፡

4. ጠቃሚ ማዕድናትን እናገኛለን፡- ማግኒዝየም፣ብረት፣ዚንክ፣ፖታሲየም እና ኮፐርን የመሳሰሉ ለሰውነታችን እጅግ ጠቃሚ ማዕድናትን ይዟል፡፡ በተለይ ሰሊነም የተሰኘው ማዕድን በብዙ ምግቦች ውስጥ አይገኝም፡፡

5. የልብ ጤናን ይጠብቃል፡- የኮሌስትሮል (የደም ቅባት) መጠንን በመቀነስ ልብን ከተለያዩ በሽታዎች ይጠብቃል፡፡

6. የደም ማነስ በሽታ (አኒሚያን) ይከላከላል፡፡ የያዘው ብረት ፣ቫይታሚን ቢ-12 እና ፎሊክ አሲድ በሰውነታችን ውስጥ የቀይ ደም ሕዋስ ምርት እንዲጨምር በማድረግ የደም ማነስ በሽታን ይከላከላል፡፡

7. ለነፍሰጡሮች እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ በፎሊክ አሲድ፣ዚያክስ አንቲን እና ፓቶጀኒክ አሲድ የበለፀገ ስለሆነ ከወሊድ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን በማስወገድ ለእናቲቱም ሆነ ለህፃኑ ጤና ጠቃሚ ነው፡፡

8. ለአይንና የቆዳ ጤንነት ይጠቅማል፡- የያዘው ቤታ ካሮሪን የቫይታሚን ኤ ንጥረ ነገር በመሆኑ የአይን ዕይታን ይጠብቃል፡፡እንዲሁም የያዘው ቫይታሚን ሲ እና ሌኮፒን ለቆዳ ጤና ጠቃሚ ነው፡፡

9. የደም ስኳርና የደም ቅባት መጠንን ይቀንሳል፡- ሁለተኛው የስኳር ሕመም ጥራጥሬዎችን የመሳሰሉ ጤናማ ምግቦችን በመመገብ መከላከል ይቻላል፡፡ ለዚህም በቆሎ አንዱ ነው፡፡

10. ለውበት መጠበቂያነት ያገለግላል፡- ከበቆሎ በዘመናዊ መንገድ ለቆዳ ልስላሴና መሰነጣጠቅ መፍትሔ የሆኑ በርካታ የቆዳ ውበት መጠበቂያዎች ተሰርተው ገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡

1. ኃይል ይጨምራል፡- የያዘው ኮምፕሌክስ ካርቦ አይድሬት ቀስ ብሎ የሚፈጭ በመሆኑ ለረጅም ሰዓታት ኃይል እንዲያገኙ ያስችሎታል፡፡ በተለይ አትሌት ወይም ጅም የሚያዘወትሩ ከሆነ በቆሎ በየእለቱ ከገበታዎ ባይጠፋ ይመከራል፡፡

እናም ምን ይጠብቃሉ ወቅቱን ጠብቆ የመጣውን የበቆሎ ቅቅልና ጥብስ በመብላት ከላይ የጠቀስናቸው የጤና በረከቶችን ለማግኘት ዛሬውን ይሞክሩት፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው!